መደበኛው የካይዘን የፅዳት መርሐ ግብር ተካሄደ!

Spread the love


==============================
ሰኔ 16/2018 (ወልቂጤ)፡ በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ተቋማዊ ባህልን ለማሳደግና ለስራ ምቹ አካባቢን ለመፍጠርና የግቢ ፅዳትና ውበት በዘላቂነት ለማስጠበቅ ታስቦ በየ15 ቀናቱ የሚካሄደው መደበኛው የካይዘን (Kaizen) የፅዳት መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የፅዳት መርሐ-ግብሩ የኮሌጁ ማህበረሰብ የግቢውን ፅዳት በዘላቂነት ከመጠበቅ ባሻገር፣ የካይዘን (Kaizen) ፍልስፍናን በመተግበር ፅዳትን ባህል ለማድረግ፣ ማራኪ፣ ሳቢ እና ውብ በማድረግ ምቹና የስራና የመማር-ማስተማር ከባቢን ለመፍጠር እንዲሁም በተቋሙ እየተተገበረ ያለውን የISO ስታንዳርድ ትግበራ በላቀ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የጉራጌ ዞን ቴ/ሙ/መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲንን ጨምሮ አጠቃላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና አስ/ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በአጠቃላይ መርሐ-ግብሩ የአንድ ጊዜ ተግባር ሳይሆን በመደበኛነት በየ15 ቀናቱ ይበልጥ በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!
—————
#ስለኮሌጃችን_ተጨማሪ_መረጃዎችን_በሚከተሉት_ሚድያዎች_ማለትም
Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.edu.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
#ሊከታተሉን_ይችላሉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *