ከማዕከላዊ  ኢትዮጵያ  ክልል  የቴክኒክና  ሙያ  ስልጠና  ቢሮ  የመጡ  የልኡካን  ቡድን  አባላት  በኮሌጃችን  ተገኝተው  የሱፐርቪዥን  ስራ  አከናወኑ።

Spread the love


ሰኔ 11/2018 (ወልቂጤ)፡ የማዕከላዊ ክልል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ የልዑካን ቡድን አባላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና በሳተላይት ካምፓሱ በመገኘት የሱፐርቪዥን ስራ አከናውነዋል።

የሱፐርቪዥኑ ትኩረት በቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ የተግባራት አፈፃፀም ላይ ሲሆን በዋናነት ደግሞ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎች ምርትና የፈጠራ ውጤቶች፣ የኮሌጁን የውስጥ ገቢን ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ የፕሮዳክሽን ስራዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ጋር ተያይዞ ከኢንተርፕራይዞች ጋር በጋራ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ነበር።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኮሌጁ የተሰሩ ስራዎችን በአካል ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፥ ባዩዋቸው አበረታችና ውጤታማ ተግባራት እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ጥቂት መስተካከልና ፍጥነት የሚፈልጉ ተግባራት ላይ በትኩረት እንዲሰራ ገንቢ የሆነ ግብረ-መልስ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በተግባር ሂደት የገጠሙ ተግዳሮቶች በኮሌጁ ዲኖች አማካኝነት ለልዑካን ቡድኑ ከቀረቡና መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ መርሐ-ግብሩ ተጠናቋል።

#ለአረንጓዴው  የኢንደስትሪ  አብዮት  እንተጋለን!
#We  Stand  for  Green  Industrial  Revolution!

#ስለኮሌጃችን  ተጨማሪ  መረጃዎችን  በሚከተሉት  ሚድያዎች  ማለትም
Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.edu.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
#ሊከታተሉን  ይችላሉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *