#የISO_21001_2018_Educational_Organization_Managment_System_ትግበራለቴክኒክኮሚቴውየሚሰጠውስልጠና_ተጀመረ።

Spread the love

ታህሳስ 14/2017 (ወልቂጤ)፡ ኮሌጃችን አለም አቀፍ የጥራት አስተዳደር ስርዓት (የISO 21001 2018 Educational Organization Managment System) ማረጋገጫን ለመተግበር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት የትግበራው አካል የሆነ ስልጠና ለኮሌጁ የISO ትግበራ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት መሰጠት ተጀመረ።

የአቅም ግንባታ ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ተወክለው በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ተከታታይ 5 ቀናትም እየተሰጠ የሚቀጥል ይሆናል።

በስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙት ቁጥራቸው 30 የሚሆኑ የISO ትግበራው #የቴክኒክኮሚቴአባላት ሲሆኑ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የሁሉም የት/ት ክፍሎች ተጠሪዎች፣ ከሳተላይት ካምፓሱ እና ደጋፊ እንዲሆኑ የተመረጡ መምህራንና ፈፃሚ ባለሙያዎችን የያዘ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *