#ኮሌጃችንበቸሃ ወረዳ ናእምድብር ከተማና አካባቢ መደበኛ ስልጠና ን በሳተላይት ማዕከል ለመስጠት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ።

Spread the love

ታህሳስ 11/2017 (ወልቂጤ)፡ ኮሌጃችን የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ታሳቢ በማድረግ #በቸሀወረዳ እና #በእምድብርከተማና_አካባቢው በሳተላይት ማዕከል ስልጠና ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ከሁለቱም አደረጃጃቶች አመራሮች ጋር አካሄደ።

የኮሌጃችን ማኔጅመንት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በኮሌጁ ም/አካ/ዲን የተመራ ቡድን ወደ አካባቢው በመሄድ ከሁለቱም መዋቅሮች አመራሮች መካከል ከእምድብር ከተማ ከንቲባና ከት/ት ጽ/ቤት እና ከቸሀ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል። በውይይቶቹም የሳተላይት የስልጠና ማዕከሉ ስራ ለማስጀመር በትኩረት እንደሚሰሩ፣ የመሰልጠኛ ማዕከሉን የማዘጋጀት ስራም እንደሚሰሩ ጠቅሰው በተጨማሪም ስልጠናው ለተለያዩ የመንግስት ሰራተኞችም ተደራሽ ቢደረግ የሚል አስተያየትም አንስተዋል።

ውይይቶቹን ሲጠቃለሉ ለአካባቢውን ማህበረሰብ ስልጠናን ተደራሽ ለማድረግ #በእምድብር_ከተማ የሳተላይት ማዕከል በዋናነት #በICT እና #በጋርመንት ሙያዎች ስልጠና ለመስጠት የስልጠና ፈላጊዎች ምዝገባ እንዲጀመር ሆኖ ኮሌጁም አስፈላጊውን የመመዝገቢያ ቅፆችን እንዲልክና የማስታወቂያም እንዲያስነግር ስምምነት ላይ በመድረስ ነው።

በዚህ መሠረት 12ኛ ክፍል አጠናቃችሁ #በመደበኛመርሐግብር መሰልጠን የምትፈልጉ ተማሪዎች እንዲሁም #በሳምንቱመጨረሻ (#ቅዳሜናእሁድ) መርሐግብር ስልጠና የምትፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከታህሳስ 14/2017 ጀምሮ #በቸሀወረዳ እና #በእምድብር_ከተማ ት/ት ፅ/ቤቶች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *