መጋቢት 03/2016 ዓ.ም፡ ኮሌጃችን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቴክኒክና ሙያ ቢሮ፣ ከኢትዮጵያ የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) እና የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለ2 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የኢንተርፕሪነርሺ (የስራ ፈጠራ) ተጠናቀቀ።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉት በ2016 ዓ.ም ከሁሉም ት/ት ክፍሎች በተለያዩ ሙያዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው የሚመረቁ ሰልጣኞች ናቸው። ስልጠናውንም በጣም ሳቢና አዝናኝ በሆነ መልኩ የሰጡት ከኢትዮጵያ የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የመጡ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ነው።
ስልጠናው አጠቃላይ ያተኮረው ሰልጣኞች ስልጠና አጠናቀው ሲወጡ በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ ስራ ፈጥረውም ሆነ ተቀጥረው ራሳቸውን ለመለወጥ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ፣ የኢንተርፕሪነርሺፕ (የስራ ፈጠራ) ፅንሰ-ሀሳብ፣ የአእምሮ ዝግጁነት (Mind set) እና የመሳሰሉ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦች ላይ ነበር።











Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0