መጋቢት 4/2016 ዓ.ም፡ የባህልና ስፖርት ሚንስትር ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮና ከወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በቆዳ እደ ጥበብ ላይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠና ማስጀመሪያው ላይ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር የእደ ጥበብ ዘርፍ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ታሪኳ ሀሰን፣ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ፣ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንዲሁም የወልቂጤ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ም/ዲን አቶ አጅመል መሀመድ ተገኝተዋል።
የስልጠናው ዋነኛ አላማ የቆዳ እደ ጥበብ ዘርፍን ማነቃቃት ሆኖ በስልጠናው የሚሳተፉ አካላት ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ ተደራጅተው እና መነሻ ካፒታል ተመቻችቶላቸው ወደ ስራ በመግባት ራሳቸውንና ማህበረሰቡን እንዲጠቅሙ ታሳቢ ያደረገ ነው።
በአጠቃላይ በስልጠናው ላይ ከጉራጌ ዞን፣ ከየም ዞንና ከቀቤና ልዩ ወረዳ የተወጣጡ ከ30 በላይ ሴቶች ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የሚሳተፉ ሲሆን ለቀጣይ ተከታታይ 10 ቀናትም የሚሰጥ ይሆናል።










Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0