#የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመሪ አሰልጣኝ መምህራን ተሰጠ
ጥር 10/2016 ዓ.ም፡ የኮሌጃችን የቴክኖሎጂ ሽግግና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን የስራ ሂደት አስተባባሪነት ከሳተላይት ማስተባበሪያ ክፍል ጋር በመተባበር ለኤ ደረጃ መሪ አሰልጣኝ መምህራን በAction Research ላይ ስልጠና ሰጥተዋል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኮሌጁ የቴ/ሽ/ኢ/ኤክስ/ም/ዲን አቶ ቦጋለ ተክሌ እንዳሉት የስልጠናው ዋና አላማ ፅንሰ-ሀሳቡን በአግባቡ ተገንዝቦ በኮሌጁ የሚስተዋሉ የተግባርና የአሰራር ማነቆዎች ለመፍታት ታሳቢ ያደረገ ነው። ከስልጠናው በኋላ በዋናነት የኮሌጁ ችግር የሆነውን የሰልጣኝ ቅበላና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጥናት የታገዘ የማስተካከያ ስራ ለመስራት ታስቧል። እንዲሁም የጥናቱን ውጤት ለሌሎችም የክላስተራችን ተቋማት በማስፋት ተጠቃሚ ለማድረግ የማስተዋቂያ መድረክ እንደሚዘጋጅ አውቀው ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል። በመጨረሻም ይህንን ጥናት የሚያስተባብሩ የተሻሉና ልምድ ያላቸውን መሪ አሰልጣኞች የመምረጥ ስራም ተሰርቷል።
ስልጠናውን በተብራራና ሳቢ በሆነ ሁኔታ የሰጡት የኮሌጁ የሳተላይት ማስተባበሪያ ክፍል አስተባባሪ አቶ ሰላሙ ይርጋለም ሲሆኑ ስልጠናውን እንዲወስዱ የተደረጉት ደግሞ ሁሉም የኮሌጃችን የኤ ደረጃ መሪ አሰልጣኝ መምህራን ናቸው።








Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0