#የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እየተሰጡ የሚገኙ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ፍላጐት እየጨመረ ይገኛል!!

Spread the love

#የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እየተሰጡ የሚገኙ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ፍላጐት እየጨመረ ይገኛል!!

ግንቦት 15/2016 ዓ.ም፡ ኮሌጃችን ከመደበኛ የስልጠና ቀናት ውጪ #በሳምንቱመጨረሻቀናት (ቅዳሜና እሁድ) ከሴክተር መ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ሙያዎች በአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎችን በመስጠት የሙያ ባለቤት እያደረገ ይገኛል።

ስልጠና እየወሰዱ ከሚገኙት መካከል ለመግለፅ ያህል በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በኩል ተደራጅተው ለመጡና ከስልጠና በኋላ የስራ እድል ተጠቃሚ ለሚደረጉ ከ65 በላይ ሴቶች #በልብስስፌት እና #በጥልፍስራ ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቀቤና ልዩ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በኩል ተደራጅተው ለመጡ ከ40 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች #በመሰረታዊየኮምፒውተርአጠቃቀም ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ የሚጠቀሱ ናቸው።

በዚሁ አጋጣሚ ኮሌጃችን የሙያ ባለቤት መሆን ለሚፈልግ ዜጎች በሚፈልጉት የሙያ አይነትና የስልጠና መርሐግብር አሰልጥኖ ብቁ ባለሙያ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ እየተጠባበቀ በመሆኑ የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *