#የTVETና የኢንዱስትሪ ትስስር ለተሻለ ውጤት
መጋቢት 11/2016 ዓ/ም፡ ኮሌጃችን ከኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የባህል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በዕደ ጥበብ ሙያ ዘርፍ በቆዳ ስራዎች ዲዛይንና ቴክኖሎጂ የተግባር ስልጠና ከመጋቢት 4/2016 ጀምሮ ሲያሳለጥናቸው የነበሩ ሰልጣኞችን ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።
በማጠናቀቂያ ፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ እንዲሁም ከፌደራል ከክልልና ከዞን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ እንግዶች የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን የዕደ ጥበብ ሙያን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው ምርት ለማህበረሠቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠበቅ፤ ዘርፉ ለወጣቶች፣ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የሥራ ዕድል የሚፈጠርና የሀገርንም ኢኮኖሚ የሚያግዝ እንደሆነ አንስተዋል።
እንዲሁም በስልጠናው የተሳተፉት አካላትም በስልጠናው በቂ እውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን ገልፀው በቀጣይ ሙያውን ወደ ተግባር በመቀየር ህብረተሰቡን በማገልገል ራሣቸውና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም ለስልጠናው መሳካት ከፍተኛ ትብብር ላደረጉ አካላት፣ ተቋማት እና ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።











Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0