#የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት 🎄🎄🎄

Spread the love

#የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት🎄🎄🎄

ጥር 10/2016 ዓ.ም፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ እንኳን ለ2016 ዓ.ም የከተራ እና የጥምቀት በዓል በፍቅር፣ በሰላም፣ በደስታና በአብሮነት አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል። በዓሉ ስናከብር ጥላቻን፣ መለያየትን፣ ዘረኝነትና ቂም በቀልን በይቅርታ፣ በአብሮነትና በፍቅር በመተካት ሰላምና ደስታ የምናነግስበት እንዲሆን ይመኛል።

የጥምቀት በዓል የትህትና፣ የፍቅርና የአንድነት ምልክት በመሆኑ እኛ የኢትዮጵያውያን ለረጅም ዓመታት ጠብቀው ያቆየናቸውን የመከባበርና የአብሮነት እሴቶች በመጠበቅና ከሀይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር ባህላዊና ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክሩ መስተጋብሮች ላይ በማተኮር ሊሆን ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ በዓሉ ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳትና በማገዝ በምድር በረከትን በሰማይ ጽድቅ የሚያስገኝ ተግባር በመሆኑ በታላቅ ትህትና ልትፈፅሙት ይገባል።

በመጨረሻም ከበዓሉ ጉን ለጎን ኮሌጃችን በ2016 የስልጠና ዘመን አስፈላጊውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ግብዓቶችን አሟልቶና አደራጅቶ በገበያው በሚፈለጉ በተለያዩ ሙያዎች በመደበኛ፣ በማታና በቅዳሜና እሁድ በአጫጭር ጊዜ እና በደረጃ ስልጠናዎች አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠንና የተከበረ ሙያ ባለቤት ሊያደርጎ እርሶን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። በመሆኑ እርሶ መጥተው እንዲመዘገቡና ሌሎችም መጥተው እንዲመዘገቡ ጥሪ እንዲያደርጉን የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን። 🙏🙏🙏

🎄🎄🎄 #በድጋሚመልካምበዓል🎄🎄🎄

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *