የISO_21001_2025_በውጭ_ኦዲተሮች_ሲደረግ_የነበረው_የኦዲት_ስራን_በስኬት_ተጠናቀቀ!!

Spread the love


==============================
ሰኔ 29/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የአሰራር ጥራቱን ለማረጋገጥና በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ በማሰብ እየተገበረው የሚገኘውን የISO 21001:2025 (Educational Organization Management System – EOMS) የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ትግበራ በውጭ ኦዲተር የማስገምገም ስራን በስኬት አጠናቀቀ።

ይህ የኦዲት ስራ ላለፉት ተከታታይ 6 ቀናት ሲከናወን የቆየ ሲሆን ስራውም የተሰራው ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ECA) በመጡ ከፍተኛ የዘርፉ ኤክስፐርቶች አማካኝነት ነው።

በዛሬ የማጠቃለያው ፕሮግራም ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ኦዲተሮቹ በ6 ቀናት ቆይታቸው ያገኟቸውን ዋና ዋና ግኝቶች የሚያሳይ አጠር ያለ ሪፖርት ለኮሌጁ ማኔጅመንት አካላትና
የት/ት ክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት አቅርበዋል። በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በኮሌጁ እና በሳተላይት ካምፓሱ የተመለከቷቸው የአሰራር ትግበራዎች በጣም ጥሩ እና አበረታች መሆናቸውን በምስጋና ገልጸዋል። በመቀጠልም ይህ የተጀመረው ጠንካራ እና ጥራቱን የጠበቀ አሰራር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የኦዲት ስራ በስኬት መጠናቀቁ ኮሌጁ የሚሰጠውን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ የኮሌጁ ማኔጅመንትና ማህበረሰብ ያለውን ቁርጠኝነት በግልፅ የሚያሳይ ነው።
——————————
#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!

#ለአረንጓዴው  የኢንደስትሪ  አብዮት  እንተጋለን!
#We  Stand  for  Green  Industrial  Revolution!

#ስለኮሌጃችን  ተጨማሪ  መረጃዎችን  በሚከተሉት  ሚድያዎች  ማለትም
Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.edu.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
#ሊከታተሉን  ይችላሉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *