#ወደ አረብ ሀገራት ለስራ ለሚሰማሩ ዜጎች የሚሰጠው የክህሎት ስልጠናተጠናክሮ ቀጥሏል!!
ግንቦት 05/2016 ዓ.ም፡ በሀገር ደረጃ ወደ አረብ ሀገራት የስራ ስምሪት ለሚያደርጉ ዜጎች የክህሎት ስልጠና እንዲሰጡና የብቃት ምዘና (COC) እንዲያስመዝኑ ብቸኛ ፍቃድ ከተሰጣቸው 72ቱ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች አንዱ የሆነው #የወልቂጤፖሊቴክኒክኮሌጅናሳተላይት_ካምፓስ ዛሬ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች ተቀብሎ የክህሎት ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
ስልጠናው ዜጎች ለስራ በሚሰማሩባቸው ሀገራት ስራቸውን በአግባቡና በጥራት እንዲሰሩ የሚያደርጋቸው ሲሆን በተጨማሪም የክህሎት ባለቤት በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን የሚያሳድግ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
በአጠቃላይ ስልጠናው ለተከታታይ 15 ቀናት በንድፈ-ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሲሆን እንደተጠናቀቀ የብቃት ምዘና (COC) በአፋጣኝ እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ፈለጓቸው ሀገራት የስራ ስምሪት እንዲያደርጉ የምናመቻች ይሆናል።






Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0