#ለገና በዓል የማዕድ ማጋራት ተደረገ

Spread the love

ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም፡ ኮሌጃችን ከጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ግምቱ ከ50 ሺህ ብር በላይ የሆነ ማዕድ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ በከተማችን ተጠልለው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የማጋራት ስራ ተሰርቷል።

በማዕድ ማጋራቱ ላይ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የኮሌጃችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ላጫ ጋሩማን ጨምሮ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ለድጋፉም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *