#ለአዳዲስ ሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተካሄደ።

Spread the love

ታህሳስ 22/2016 ዓ.ም፡ በዚህ የሥልጠና ዘመን በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው የመደበኛ ስልጠና ለመውሰድ በኮሌጃችን ከተመዘገቡ ሰልጣኞች መካከል የICT ሙያ ለመሠልጠን የተመዘገቡት ከፍተኛ ቁጥር ስለነበራቸውና በICT ሙያ የምንቀበላቸው ሰልጣኞች ቁጥር ውስን ስለሆነ ተማሪዎቹ ግንዛቤ አግኝተው ሌሎች በኮሌጁ በሚሰጡ የሙያ ዘርፎች ፍላጎታቸውን እንዲያስተካክሉ በማሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ተካሂዷል።

በመርሐግብሩ ላይ ከሁሉም ት/ት ክፍሎች በመጡ አሰልጣኝ መምህራንና የየት/ት ክፍሎች ተጠሪዎች አማካኝነት በየሙያዎቹ ላይ የተብራራ ገለፃ ተደርጓል። በቀረቡት ገለፃዎች ላይ ተሳታፊ ተማሪዎች ግልፅ ያልሆኑላቸውን ጥያቄዎች ጠይቀው ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በአጠቃላይ ከግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብሩ በኋላ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ወደ ሌሎቹ አዋጪ የሙያ ዘርፎች ቀይረው ለመሰልጠን ፍላጎት ማሳየት ችለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *