ከፌዴራልበመጡየልዑካንቡድንአባላትሱፐርቪዥንተደረገ

Spread the love

========================================

ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም፡ ከፌደራል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የመጡ የልኡካን ቡድን አባላት በኮሌጃችን በመገኘት የሱፐርቪዥን እና የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት ባዘጋጁት ቼክ-ሊስት አማካኝነት ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ እንዲሁም የመረጃዎችን እይታና ግምገማ ካደረጉ በኋላ በተመረጡ ት/ት ክፍሎች በመዘዋወር ምልከታ አድርገዋል። በዚህም ሂደት ስልጠና ላይ የነበሩ አሰልጣኝ መምህራንንና ሰልጣኞችን በማነጋገር አስፈላጊውን መረጃ እንዲወስዱ ተደርጓል።

ከገለፃውና ከጉብኝቱ መነሻነት የልዑካን ቡድኑ አባላት ግብረ-መልስ ሰጥተዋል። በጠንካራ ጎኑ ከሰጡን መካከል፦ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራትን በእቅድ መፈፀም መቻሉ፣ ተቋሙን የኢንተርፕሪነርሺፕ ማዕከል ለማድረግ፣ ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ፣ ምድረ-ግቢውን ምቹና ለስልጠና ተስማሚ ለማድረግ፣ ተቋሙን ከማሰልጠን በላይ እሳቤን ለመተግበር የምርት ማዕከል ለማድረግና ዲጂታላይዜሽንን ለማስፋፋት የተከናወኑ ተግባራት በተጨማሪም ከክላስተር ኮሌጆች ጋር ያለን የጠበቀ ግንኙነትና የተግባር መደጋገፍ፣ በልዩ ሁኔታ ደግሞ የተጠናከረ የቦርድ ድጋፍ መኖሩ፣ በቂም ባይሆን የሰልጣኞች ቅበላ መጀመሩና ምዝገባውም ዲጂታላይዝ መደረጉ፣ የምንሰራቸው ቴክኖሎጂዎች የማህረሰባችን ችግር መሠረት ያደረጉ መሆናቸው፣ የሀገር በቀል እውቀትን ለማሳደግ ፣ የተቋሙን አቅም ለማሳደግ ከረጂ ድርጅቶች፣ ከባለድርሻና ከትኩረት ዘርፍ መሪ መስሪያ ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ላይ በዋናነት አስተያየት ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአንዳንድ የተግባራቶች አፈፃፀም ላይ ክፍተቶች የሚስተዋሉና በተሟላ ሁኔታ እየተከናወኑ ያለመሆናቸው በመግለፅ በቀጣይ ጊዜያት ተጠናክረውና ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ እንደሚገባ ገንቢ አስተያየት ሰጥተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *