የህዳርበዓላትበጋራ_ተከበሩ

Spread the love

====================

ታህሳስ 04/2016 ዓ.ም፡ በኮሌጃችን በየአመቱ የሚከበሩት የህዳር በአላት በተለያዩ አስተማሪ መርሐግብሮች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በጋራ የተከበሩት በዓላት (1ኛ) የፀረ-ኤድስ ቀን ለ35ኛ ጊዜ “

የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ HIV መከላከያ” በሚል መሪ ቃል፤ (2ኛ) የፀረ-ሙስና ቀን ለ20ኛ ጊዜ “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው! በጋራ እንታገለው!” በሚል መሪ ቃል፤ (3ኛ) የነጭ ሪቫን ቀን ለ18ኛ ጊዜ “መቼም የትም በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንልም!!!” በሚል መሪ ቃል፤ እንዲሁም (4ኛ) የአካል ጉዳተኞች ቀን ለ22ኛ ጊዜ ናቸው።

በበዓሉ ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ አሰልጣኝ መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞችና ሰልጣኞችም ተሳትፈዋል።

በዓላቱ በጋራ ሲከበሩ በዋናነት በፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን መጀመሪያ በዓላቱን አስመልክተው የተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች በተወከሉ የኮሌጁ ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች አማካኝነት እንዲቀርብ ተደርጓል። በመቀጠልም በቀረቡት ሰነዶች መነሻ የበዓላቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ገንቢና አስተማሪ አስተያየቶችን እንዲሁም ግልፀኝነት የሚያስፈልጋቸውን ጥያቄዎች ደግሞ ተነስተው ጥልቅ ውይይትና ምላሽ ተሰጥቶባቸው መግባባት ላይ በመድረስ እና የትግሉ አካል መሆናቸውን በማረጋገጥ ውይይቱ ተጠናቋል።

በመጨረሻም የሴቶችን ጥቃት አወግዛለሁ ለትግሉም አጋር እሆናለሁ በሚል የሚከበረው የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ የበዓሉ ተሳታፊ የነበሩት ወንዶች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እናወግዛለን!!! የትግሉ አጋር እንሆናለን!!! በሚል የቃለ-መሀላ ስነ-ስርዓት ተደርጎ የበዓሉ መርሐግብር ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *