#ክላስተራዊ_የስልጠናና_የምክክር_መድረክ_ተካሄደ።

Spread the love

===================================

ህዳር 17/2016 ዓ.ም፡ ክላስተራዊ የስልጠናና የምክክር መድረክ በኮሌጃችን ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ አጠቃላይ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዲኖችና ም/ዲኖች፣ የጉራጌ ዞን ቴ/ሙ/ት/ሥ/መምሪያ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የኮሌጃችን የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና የየት/ት ክፍል ተጠሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

መድረኩ በጉራጌ ዞን ቴ/ሙ/ት/ሥ/መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ሰርገማ የመክፈቻ ንግግር ተጀምሯል። በመቀጠልም ለመድረኩ የተዘጋጁ ከፌደራል በክላስተሩ አስተባባሪ ኮሌጅ በኩል የወረዱና በስልጠና የተላለፉ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበዋል። በዚህም መሠረት የ21ኛው ክፍለ ዘመን አመራር (የቀውስ ጊዜ አመራር)፣ የPublic Enterprnurship እና የቴ/ሙያ የውጥ ጉዞን የተመለከቱ ሰነዶች በክላስተሩ አስተባባሪና የኮሌጃችን ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን ቀርበዋል። ሌላው ከስልጠና በላይ የሚለው የሪፎርም ሰነድ ደግሞ በኮሌጃችን ም/አካ/ዲን በአቶ አጅመል መሐመድ አማካኝነት ከቀረበ በኋላ በሰነዶቹ ላይ ውይይትና ጥያቄዎች ከስልጠናው ተሳታፊዎች ቀርበው በመድረኩ መሪዎች አስተያየትና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ሌላው የእለቱ መድረክ አጀንዳ የነበረው የ2015 የስራ ዘመን የክላስተሩ እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ከስልጠናው ተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርቦ ከክላስተሩ አስተባባሪዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል። በመጨረሻም በተዘጋጀው የ2016 የስራ ዘመን የጋራ እቅድ ላይ ሁሉም የክላስተሩ ኮሌጆች ጋር በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *