=================================
ህዳር 27/2016 ዓ.ም፡ የኮሌጃችንን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የንቅናቄ መድረክ አካሂደናል።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢና የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የጉራጌ ዞን የቴ/ሙ/ት/ሥ/መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ሰርገማን ጨምሮ ኮሌጃችን በሚሸፍናቸው የ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች (የወልቂጤና እምድብር) ከንቲባዎች፣ የመንግስት ዋና ተጠሪዎች፣ የኢንተፕራይዞችና የስራ እድል ፈጠራና ትምህርት ፅ/ቤቶች ኃላፊዎች፣ የ2ቱ ወረዳዎች (ቸሃና አበሽጌ) እንዲሁም የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የመንግስት ዋና ተጠሪዎች፣ የኢንተፕራይዞችና የስራ እድል ፈጠራና ትምህርት ፅ/ቤቶች ኃላፊዎች፣ የኮሌጁ የቦርድ አባላት፣ ኮሌጃችን በሚሸፍናቸው አካባቢዎች ስር የሚገኙ የ20ዎቹ 12ኛ ክፍል ፈተናን ያስፈተኑ ት/ቤቶች ር/መምህራን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ የአካባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የዞን መምሪያ እና የኮሌጃችን የማኔጅመንት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
መድረኩ ጅማሮውን ያደረገው የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን አማካኝነት ባቀረቧቸው ሁለት የመወያያ ሰነዶች ሲሆን በቀረቡት ሰነዶች መነሻነት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪና በኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ላጫ ጋሩማ መድረክ መሪነት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አካላት በርካታ ገንቢ አስተያየቶች የሰጡ ሲሆን ለአብነት ለመጥቀስ ያህል ኮሌጁ ራሱን ለማህበረሰቡ ከማስተዋወቅ አንፃር ዝቅተኛ በመሆኑ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት፣ ተማሪዎች ወደ ኮሌጁ በበቂ ሁኔታ የማይመጡበትን ምክንያት በአግባቡ በጥናት በማረጋገጥ የማስተካከያ ስራዎች መስራት እንዳለበት፣ ከዚህ በፊት ወደ በኮሌጃችን ሰልጥነው የወጡ ሰልጣኞች ከስራ ጋር ከማስተሳሰር ጋር በትኩረት መስራትና ውጤታማ የሆኑትንም ደግሞ የማስተዋወቅ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ፣ በመሠረታዊነት በTVET ላይ ያለው የማህረሰቡ ዝቅተኛ አመለካከት ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋርም ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በጣም የጠበቀና ውጤታማ ማድረግ ላይ መሰራት እንዳለበት፣ ለየመዋቅሩ ያሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን መረጃ በአግባቡ ለይቶ ሊሰራ እንደሚገባ እና ሌሎችም ገንቢ አስተያየቶች አንስተዋል። በተጨማሪም የዞኑ ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል ስራው በፖለቲካው ዘርፍ አንዱ የማታገያ አጀንዳ ተደርጎ በቀጣይ 15 ቀናት በትኩረት እንደሚሰራ የንቅናቄው መድረኩ ግብ የሆነውን ጉዳይ በማንሳት ሀሳብ ሰጥተዋል።
በመቀጠልም የዞናችን ዋና አስተዳዳሪና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ላጫ ጋሩማ መድረኩን ሲያጠቃልሉ የንቅናቄ መድረኩ ግብ የሆነው አጠቃላይ የዕለቱ የመድረኩ ተሳታፊዎች በየአካባቢያቸው የሚገኙ ተማሪዎች ግንዛቤ በመፍጠርና በመጠርነፍ ወደ ኮሌጃችን መጥተው የሙያ ባለቤት ሆነው ከስራ ጋር እንዲተሳሰሩ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት፣ በየመዋቅሩ የሚገኙ የመንግስት ተጠሪዎች በቀጣይ 15 ቀናት ጉዳዩን ዋና አጀንዳ አድርገው በመስራት ተማሪዎችን ወደ ኮሌጅ እንዲያስገቡ እንዲሁም ኮሌጃችንም ለሚመጡ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ ማሳሰቢያና የስራ መመሪያ ሰጥተው ውይይቱን አጠቃለዋል።
በመጨረሻም የንቅናቄ መድረኩ ግቡን እንዲመታ በማሰብ ከተሳታፊዎች በተውጣጡ አካላት የተዘጋጀውን ባለ6 ነጥቦች የአቋም መግለጫ በእምድብር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በአቶ ግንባሩ በርጋ አማካኝነት ቀርቦ መድረኩ ተጠናቋል።









Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0