የክረምትበጎፍቃድአገልግሎትተጠናክሮ_ይቀጥላል!!!
ኮሌጃችን በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በከተማ አስተዳደሩ የአንድ አቅመ ደካማ ቤት ለመገንባት ርክክብ አደረገ።
በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙባረክ አሕመድ በፍቃደኝነት የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት የህሊና እርካታን ይሰጣል ብለዋል። ኮሌጃችንም የአቅመ በደካማ ቤት ለመገንባት ፍቃደኛ በመሆኑ አመስግነው መሰል በጎ ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
የኮሌጃችን የበጎ አድራጎት አስተባባሪ ወይዘሮ ሊዲያ ሳኒ በዚህ ወቅት እንዳሉት ኮሌጁ ቀደም ባለው ጊዜም የተለያዩ በጎ ስራዎችን እንደሚሰራም ገልፀው በዘንድሮው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካማዋ ቤት ለመገንባት ርክክብ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ቤቱን ለመገንባት ቃል በመግባቱ ደስተኛ እንደሆኑም ተናግረው የቤት ግንባታውም አጠናቆ ለማስረከብ በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ ጴጥሮስ አስራት ኮሌጁ በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ከተማ አስተዳደሩን እንደሚያግዝ ተናግረዋል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ የአንድ አቅመ ደካማ ቤት ለመገንባት ቃል ገብቶ ርክክብ መደረጉን ጠቁመው በበጎ ፍቃድ የሚሰራ ስራ ውለታው በፈጣሪ ዘንድ እንደሚገኝ ነው የገለፁት።
በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በበኩር ክፍለ ከተማ እድገት በር ቀበሌ ቤታቸው የሚታደስላቸው ወይዘሮ ሽታዬ አባተ ህይወታቸውን በብዙ ችግር እያሳለፉ መሆኑን ተናግረው ቤታቸው በአዲስ መልክ እንዲገነባ በመደረጉ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል።










Users Today : 0
Total Users : 7601
Views Today :
Views Yesterday : 13
Views Last 7 days : 84
Views Last 30 days : 446
Views This Month : 338
Views This Year : 4561
Total views : 31016
Who's Online : 0