#ሀሰተኛየትምህርት ማስረጃዎችን በጋራ እንከላከል!!!

Spread the love

#ሀሰተኛየትምህርት ማስረጃዎችን በጋራ እንከላከል!!!

መጋቢት 24/2016 ዓ.ም፡ የማ/ኢ/ክ/መንግስት የቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ በስሩ በሚተዳደሩ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ስር የሚገኙ የሰው ኃይሎች የትምህርትና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃዎች ማጣራት ስራ ላይ ለኮሌጃችን ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ አላማ የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 06/2016 መሠረት የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ የሚፈፀም ቅጥር፣ የደረጃ እድገት፣ የደሞዝ ጭማሪ ወይም ሌላ ጥቅማ ጥቅም በዲስፕሊንና በወንጀል ተጠያቂነት በየደረጃው በሚገኙ አካላት ላይ እንደሚወስድና ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተደንግጓል።

በድንጋጌ መሠረት የኮሌጁን ኃላፊዎች፣ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የትምህርትና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃቸው ተጣርቶ እንዲቀርብ መንግስት ባስቀመጠው ጥብቅ አቅጣጫ መሠረት የማጣሪያ ስራ ለመጀመር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ተዘጋጅቷል።

በመድረኩም ላይ አጠቃላይ የኮሌጁ ኃላፊዎች፣ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *