#የቦርድአባላትግምገማናየመስክምልከታ!!!

Spread the love

#የቦርድአባላትግምገማናየመስክምልከታ!!!

ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም፡ የኮሌጁ የቦርድ አባላት በኮሌጃችን በመገኘት ግምገማና የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

የቦርዱ ሰብሳቢና የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማን ጨምሮ ሌሎች የቦርድ አባላት በተገኙበት ግምገማና የመስክ ምልከታው የተካሄደ ሲሆን በግምገማው ላይ የኮሌጁ የ2015 የስራ ዘመን እቅድ አፈፃፀም እና የ2016 የስራ ዘመን መነሻ ጠቋሚ እቅድ በኮሌጁ ዲን በአቶ ኸይሩ አህመዲን አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። ተሳተፊ የቦርድ አባላት በሰጡት አስተያየት የእቅድ አፈፃፀሙ በአጠቃላይ የተሻለ እንደሆነ ገልፀው በአንዳንድ ተግባራት ላይ ግን የሚታዩ ዝቅተኛ አፈፃፀሞች በቀጣይ በትኩረት ተይዘው ሊተገበሩ እንደሚገባ አሳስበዋው። በተጨማሪም ግልፀኝነት በሚፈልጉ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ ደግሞ የኮሌጁ ዲኖች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

ከውይይቱ በመቀጠል የመስክ ምልከታ የተካሄደ ሲሆን በዚህም አንዳንድ ስልጠና ክፍሎች እየተሰሩ ያሉ የአቅም ግንባታ፣ ጥራት ማረጋገጥ (KAIZEN) እና አቅምን ለማጎልበት እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በማጠቃለያው የቦርድ አባላቱ ኮሌጁን በአስፈላጊው ነገር ለመደገፍና የገጠሙ ችግሮች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን በማረጋገጥ የመርሐግብሩ ማብቂያ ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *