#የማህበረሰባችንን ተጠቃሚነት የሚያደርጉ የበጎ አድራጎት ተግባራትን የመደገፍ ስራችንን አጠናክረን_እንቀጥላለን!!!👍👍👍

Spread the love

ሀምሌ 07/2015 ዓ.ም፡ የዞናችን የ2015 ዓ.ም የበጋ ወራት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የመክፈቻ ፕሮግራም በአገና ከተማ በተካሄደበት ወቅት ኮሌጃችን ለአገልግሎቱ መሳካት ላደረገው አስተዋጽኦ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪና የኮሌጃችን የቦርድ ሰብሳቢ #አቶላጫጋሩማ በኩል #የምስጋናየምስክርወረቀት ተበርክቶለታል።

ኮሌጃችንም ለተበረከተለት እውቅና ልባዊ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይም የማህበረሰባችንን በተለይም የወጣቶች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ነባር የመረዳዳት ባህላችን የሚያዳብሩበት፣ መንግስት የማይደርስበት የልማት ክፍተቶችን የሚሸፍኑ፣ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው የሚያጠናከሩና ሌሎችም ከፍተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ በበጋና በክረምት ለሚካሄዱ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች የማገዝና የመደገፍ ተግባራችንን አጠናክረን የምናስቀጥል ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *