SNNPRs Government Communication Affairs Bureau

Spread the love

  · 

ጥቅምት 5/2015

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለኢንደስትሪ ልማት ወሳኝ ነው ተባለ።

ሲካሄድ የዋለው የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የ2014 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2015 እቅድ የዝግጅት ምእራፍ ክልል አቀፍ ሴክተር ጉባኤው ተጠቃለለ።

የ2014 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸምና የ2015 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ቢሮው በበጀት አመቱ የተከናወኑ በድክመት የታዩ ክፍተቶችን በመገምገም በጥንካሬ የተነሱትን በመለየት ለቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

ከተመዘገቡ ስኬቶች በዋናነት ቢሮው ከተጠሪ ተቋማት እና ከሌሎች ከልማት መስሪያ ቤቶች ጋር በመሆን የልማት ኮሪደርን መነሻ በማድረግ 11 የእሴት ሰንሰለት ትንተና ጥናት ማካሄዱንና የስልጣን የመብት ምጣኔ ከ63 ወደ 67 ማሳደግ መቻሉ ገልጿል።

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የግል ኮሌጆች በስልጠናና በምዝና የሚታዩትን ብልሹ አሰራሮች ለማረም ጥረት ተደርጓልም ተብሏል።

የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የነበሩና ለረዥም ጊዜ ሲጓተቱ የነበሩ ጉዳዮችን የክልሉ መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠትና ከ500 ሚልዮን ብር በላይ በመመደብ 13 ኮሌጆችን ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ለ 2015 በጀት አመት ስልጠና ዝግጁ መደረጉም ተብራርቷል።

የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ከዞንና ከልዩ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያና ጽ/ቤት ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ2012 ባወጣው መመሪያ እና በቢሮው ባሳዩት ትጋት በ2014 በጀት አመት በተቋሙ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሶስት ሰራተኞች የእውቅናና የማትጊያ ሽልማት በመስጠት ጉባኤውን አጠናቋል።

በሰናይት አካሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *