በ2014 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዕውቅናና ሽልማት መስጠቱን የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ገለጸ፡፡
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለሁለተናዊ ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ መድረክ ላይ የተሻለ አፈጻጸም ላላቸው ተቋማት ቢሮው ዕውቅናና ሽልማት ሰቷል፡፡
በ2014 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያዎች፣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና አንድ ልዩ ተሸላሚ መሆን ችለዋል፡፡
በ2014 በክልሉ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያዎች መካከል የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ 1ኛ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ 2ኛ የጋሞ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ 3ኛ የስልጤ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ሲሆኑ የየም ልዩ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ልዩ ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ በ2014 ዓ.ም ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መካከል የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ 1ኛ ጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2ኛወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 3ኛ ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመሆን ሽልማታቸውን ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል፡፡
ብቁና ተነሳሽነት ያለው ስራ ፈጣሪ ዜጋን እንፈጥራለን!
ዘገባው፦ የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።




Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0