ጥቅምት 06/2015 ዓ.ም (ወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬዲዮ)
ሰልጣኞች ባገኙት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰረት ስራቸውን በጥራትና በውጤታማነት መስራት እንዳለባቸው የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ።
ኮሌጁ ከግብርና፣ ከኢንተርፕራይዝ፣ ከምርጥ ዘር ምርምርና ከክላስተር ኮሌጆች ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን በስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ እንዳሉት የቴክኒክና ትምሀርትና ስልጠና ተቋማት ትውልድ ተሻጋሪ ተግባራት ይከውናሉ።
በመሆኑም የሚሰጠው ሁሉን አቀፍ ስልጠና ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ አዲስ የስልጠና ካሪኩለም ተዘጋጅቶዋል ያሉት ዲኑ ባለሙያውም ስለ ሚሰራው ስራ በቂ ክህሎት ሊኖረው እንደሚገባና ስልጠናውም ይህንኑ ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል።
የስራ አፈጻጸም በጥራት ለመገምገም የሚሰጠው ቴክኒካል ስልጠና ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም ሰልጣኞችም ባገኙት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰረት ስራቸውን በጥራትና በውጤታማነት መስራት እንዳለባቸውም ነው አቶ ኸይሩ ያሳሰቡት።
በተለይም መንግሰት የሚሰጠው ሃብት በቂ አለመሆኑንና ኮሌጆችም አሁን ያለው የዋጋ ንረት ስልጠናቸው ላይ ውስንነት እንዳይፈጥር እቅድ አዘጋጅተው ከተለያዩ ድርጅቶች ገር ትስስር በመፍጠር ሃብት የማፈላለግ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል።
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አቶ ቦጋለ ተክሌ እንዳሉት ሁሉም በየደረጃው ያለ አካል ግብ አድርጎ የሚሰራው ሃገርን ብሎም ማህበረሰቡን ለመለወጥ እንደመሆኑ ስራዎችም ውጤታማ በሆነ መልኩ መስራት ተገቢ ነው ።
ግብርና መር የሆነው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ ኢንደስትሪ መር ለመቀየር እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ በአሰራር ሂደቱ ላይ የሚፈጠሩ ክፍተቶች መቅረፍ ተገቢ መሆኑን ጠቁመው ለዚህ ደግሞ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ሚናቸው የጎላ መሆኑንና ሌሎች ሴክተሮችም ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስረድተዋል።
የሚፈጠሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ለተጠቃሚው ተደረሽ ከማድረግ በተጨማሪ ማህበረሰቡም ቴክኖሎጂን በፍጥነት ተላምዶ ተግባር ላይ ማዋል ይጠበቅበታል ነው ያሉት።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠና መዘጋጀቱ በየዘርፉ ያሉ ችግሮች አይቶ ለመቅረፍ እንደሚያስችልና በዚሁ የአቅም ግንባታ ስልጠናም ስራቸው በተገቢው እንዲከውኑ የሚያስችል አውቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ከሃብት ማመንጨት፣ ከኢንተርፕራይዝ ድጋፍ ፣ ከቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ከአዲሱ የስልጠና ካሪኩለምና ሌሎቸም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩም ገልጸዋል።
ስልጠናውን የሰጡት በኮሌጁ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂስት ሚሊዮን አለሙ የተሰጠው ስልጠና ችግሮች ላይ ትኩረት ያደረገ በመሆኑ ሁሉም ሚናው እንዲያውቅ ያደርጋል ብለዋል።
ዘጋቢ፣ አማን ቢካ





Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0