#ተመራቂ_ሰልጣኞችን_ከሥራ_ጋር_ማስተሳሰር_ታሳቢ_ተደርጎ_ሲሰጥ_የነበረው_የአቅም_ግንባታ_ስልጠና_ተጠናቀቀ።
=============================
መስከረም 22/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አካላት ጋር በመተባበር፣ በምልመላ ፈተና ከተመረጡ የ2018 ዓ.ም. ተመራቂዎች መካከል ለተሳተፉ ሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስልጠናው በኮሌጃችን ውስጥ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ዓላማውም ተመራቂዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ለሚያከናውኑት የስራ ተግባር የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ክህሎት ማጎልበት ታሳቢ ያደረገ ነበር። ስልጠናው ለአራት ተከታታይ ቀናት ከፌዴራል በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት በተግባርና በንድፈ-ሀሳብ የተሰጠ ሲሆን ከስልጠናው በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሰልጣኞቹ ወደ የተመደቡበት አካባቢ በመሄድ ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ ይሆናል።
በአጠቃላይ ኮሌጁ የሙያ ስልጠና ከመስጠት ባሻገር ተመራቂ ሰልጣኞችን ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ ዋነኛ ተግባሩ አድርጎ እየሰራበት የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ይህንን ተግባር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ ከመንግስት ተቋማትና ከግሉ ዘርፍ ተቋማትና ሌሎችም ጋር በመቀናጀት አጠናክሮ የሚያስቀጥል ይሆናል።
#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!




Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0