#የኢንፎርሜሽን_መረብ_ደህንነት_ኤጀንሲና_የቼቼ_ቴክኖሎጂ_ኩባንያ_ልዑካን_ኮሌጃችንን_ጎበኙ።

Spread the love

#የኢንፎርሜሽን_መረብ_ደህንነት_ኤጀንሲና_የቼቼ_ቴክኖሎጂ_ኩባንያ_ልዑካን_ኮሌጃችንን_ጎበኙ።
==================================
መስከረም 12/2019 (ወልቂጤ)፡ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና ከቼቼ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በመገኘት ጉብኝት አደረጉ።

የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የተዘጋጀው በጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያና በወልቂጤ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ሲሆን፣ በልዑካን ቡድኑ ውስጥ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ስራዎች ከፍተኛ እውቅና ያተረፉ በርካታ ወጣቶችም ተካተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የት/ት ክፍሎችን የተግባር ማሰልጠኛ ቦታዎችን እና የፈጠራ ስራዎች የሚከናወኑባቸውን ክፍሎች በመዘዋወር ጎብኝተዋል። በዚህም ወቅት በኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን እንዲሁም በየት/ት ክፍሎቹ ኃላፊዎች አማካኝነት ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል። በዚህም ጉብኝት በስልጠና፣ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለወጣቶቹ የልምድ ልውውጥና የትብብር መድረክ መፍጠር ችሏል።

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ አባላት በኮሌጁ ባዩት አጠቃላይ የስራ አቅም በማድነቅ በጉብኝቱ መደሰታቸውንና በቀጣይ በጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *