Spread the love

#የ2018_የአረንጓዴ_አሻራ_የችግኝ_ተከላ_መርሐ_ግብር_ተካሄደ።
==============================
ሐምሌ 24/2018 (ወልቂጤ): “#ተስፋን_እንትከል!” በሚል ቃል የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የ2018 “የአረንጓዴ አሻራ” የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብርን በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ፈንጣ ቀበሌ ላይ አካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ መምህራን፣ አስ/ሠራተኞች እንዲሁም በኮሌጁ መደበኛና በክረምት የአጫጭር ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በንቃት በመሳተፍ ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

ይህ የመጀመሪያ ዙር የችግኝ ተከላ መርሐግብር ሲሆን ከ2,000 በላይ ሀገር-በቀል ችግኞች ተተክለዋል። የተተከሉት ችግኞች የአካባቢን ሥነ-ምህዳር ለመጠበቅ፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ አካባቢ ለማስረከብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ናቸው።

በተጨማሪም ይህ የተከናወነው ሥራ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የመጀመሪያ ዙር ሲሆን፣ በቀጣይ ዙሮች ቀሪ ችግኞች በኮሌጁና በሳተላይት ካምፓሱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የመትከል ስራው የሚቀጥል ይሆናል።

#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *