#አመታዊ የተቋም የክህሎት የቴክኖሎጂና የጥናትና ምርምር ውድድር _ ተጀመረ !!!

Spread the love

#አመታዊ የተቋም የክህሎት የቴክኖሎጂና የጥናትና ምርምር ውድድር _ ተጀመረ !!!

ግንቦት 04/2016 ዓ.ም፡ በየአመቱ በተቋም ደረጃ የሚካሄደው #የክህሎትየቴክኖሎጂናየጥናትናምርምርውድድር መካሄድ ጀመረ።

በመክፈቻ መርሐ-ግብሩ ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ ተወዳዳሪ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች እንዲሁም ለዳኝነት የተመረጡ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት (የወልቂጤ ሳተላይት ካምፓስ) መምህራንም ተገኝተዋል።

የውድድሩ አላማ በተቋሙ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ሰልጣኞች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ፣ ስልጠና የሚሰጡ አሰልጣኞች ያሉበትን የክህሎት ደረጃና የክህሎት ክፍተታቸውን እንዲለዩና በመካከላቸውም የውድድር መንፈስን ለመፍጠር እንዲሁም በዓመቱ በሰልጣኞች፣ በአሰልጣኞችና በኢንተርፕራይዞች የተሰሩ የህብረተሰባችንን ችግር የሚፈቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማወዳደርና በመገምገም እውቅና ለመስጠት ታሳቢ ያደረገ ነው። ከነዚህ በተጨማሪ በቀጣይ በየደረጃው በክላስተር፣ በክልል እንዲሁም በፌዴራል ደረጃ ለሚካሄዱ መሠል ውድድሮች ላይ ኮሌጃችንን ወክለው የሚሳተፉ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች እንዲሁም የቴክኖሎጂዎችና የጥናትና ምርምር ስራዎች ለመለየት ነው።

ውድድሮቹ ፉክክራቸውን ጠብቀው ለቀጣይ ተከታታይ 3 ቀናት የሚካሄዱ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *