#ADRA_Ethiopia_የGreen_Energy_TVET_ፕሮጀክትከ ኮሌጃችን ጋር ያለው ጠንካራ በርካታ_ትብብር

Spread the love

#ADRA_Ethiopia_የGreen_Energy_TVET_ፕሮጀክትከኮሌጃችንጋርያለው ጠንካራ በርካታ_ትብብር

ግንቦት 22/2016፡ በኮሌጃችን የሚገኘው የADRA Ethiopia የ”Green Energy TVET” ፕሮጀክት ከኮሌጃችንና ከጉራጌ ዞን የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች መምሪያ ጋር በመተባበር በ1ኛ ዙር #በሶላር_ኢነርጂ አጫጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

ADRA Ethiopia በ”Green Energy TVET” ዘርፍ #በሶላር_ኢነርጂ ላይ እየሰራ የሚገኝ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ሲሆን ከኮሌጃችን ጋር በመተባበር ስልጠናው ለሁሉም ለዜጎች በነፃ እንዲዳረስ ለማድረግ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች፣ ለአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ድጋፎችን እየሰጠ እንደሚገኝ የፕሮጀክት ማኔጀር አቶ ኤፍሬም ገልፀዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሰልጣኞቹ እየተሰጠ ያለው ስልጠና የድጋፉ አካል መሆኑንና ስልጠናው የንግድ ስራና የግብይት ስራ አመራር ሂደቶች፣ የውስጥ አደረጃጀትና የንግድ ስራን ማሳደግ፣ የንግድ ትስስር፣ የአዋጭነት ሰነድ (Business Plan) አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሌጁ ም/ዲን አቶ አጅመል መሀመድ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ በሚፈልገውና እየጨመረ በመጣውን #የሶላር_ኢነርጂ ሙያን ለማስፋት ለኮሌጃችን የስልጠና መሳሪያዎች በማቅረብና ለአሰልጣኝ ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሀሳባቸውን ሲያጠቃልሉ በቀጣይ ከፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለ2ኛ ዙር በሙያው የአጫጭር ጊዜ ስልጠና ለሁሉም ዜጎች በነፃ ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅቱን ያጠናቀቀ በመሆኑ መጥታችሁ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *