#በኢትዮጵያ የስራገበያ መረጃ አሞላል ላይ ስልጠና_ተሰጠ!!
ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ፣ የጉራጌ ዞን የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ እና የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ከኮሌጃችን ጋር በመተባበር ለኮሌጁ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና አስተዳደር ሰራተኞች በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው ከፌዴራል የስራና ክህሎት ሚኒስትር በመጡ የዘርፉ ባለሙያ ሲሆን በስልጠናው ላይ የዞኑ የቴክኒክና ሙያ እና የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያዎች ኃላፊዎች እንዲሁም የኮሌጃችን ዲኖችና የማኔጅመንት አባላትም ተገኝተዋል። የስልጠናው አላማ ሁሉም እድሜው ከ15-64 የሆነ ዜጋ በዚህ መረጃ ስርዓት ውስጥ ተመዝ የተሻሉ የስራ አማራጮች እንዲያገኝ እድል የሚፈጥር መሆኑን ተገልጿል።











Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0