#የፌደራል ናየክልል አመራሮችየመስክ ምልከታ

Spread the love

#የፌደራል ናየክልል አመራሮችየመስክ ምልከታ

ሚያዝያ10/2016 ዓ.ም፡ በፌዴራል የስራና ክህሎት ሚኒስትር የክህሎት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራና በስሩ የፌደራል ተቋማት ኃላፊዎችና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቴክኒክና ሙያ፣ የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞችና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች ኃላፊዎች የያዘ የሱፐርቪዥን ቡድን በኮሌጃችን በመገኘት የመስክ ምልከታ አደረገ።

የመስክ ምልከታው የተጀመረው የኮሌጃችን የቦርድ ሰብሳቢ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዋና አማካሪና ተወካይ አቶ ዳርጌ ተክሉ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ነው። በመቀጠልም የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን በለውጥ ስራዎች የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎችን ገለጻ አድረገዋል። በገለፃው ኮሌጁን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እና ከማሰልጠን በላይ እሳቤን ለመተግበር ከግንዛቤ ፈጠራ ጀምሮ የውስጥ ገቢን በማሳደግ የኮሌጁ በጀት ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን ህጋዊ ኢንተርፕራይዝ ተቋቁሞ እየተሰሩ መሆኑን፤ የአካባቢን ፀጋ መሰረት በዞኒንግና ዲፈረንሼሽን 5 ሙያዎች ተመድቦ እቅድ አዘጋጅቶ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና ሌሎችም ቁልፍ ተግባራት አንስተዋል፡፡

ከገለፃው በኋላ የሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት የተከናወኑ ስራዎችን የአካል ምልከታና ጉብኝት አድርገዋል። በገለፃውና በአካል ምልከታው መነሻነት በኮሌጁ የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እንደጅምር አበረታች መሆናቸውንና ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አንስተው በሌላ በኩል ደግሞ ኮሌጁን ለስራ ምቹና ሳቢ ከማድረግና የውስጥ ገቢን በሚጠበቀው ደረጃ ከማሳደግ አንፃር የተሰሩ ሰራዎች በልዩ ትኩረት ተሰርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊስተካከሉ እንደሚገባ አሳስበው የመስክ ምልከታ መርሐ-ግብሩ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *