የአቅምግንባታስልጠናው_ተጠናቀቀ።

Spread the love

============================

ህዳር 21/2016 ዓ.ም፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የመካኒክስ እና የኤሌክትሮ መካኒካል የማሽነሪ ጥገናና አስተዳደር ስልጠና ላይ ተሳትፈው በመጡ የኮሌጃችን አሰልጣኝ መምህራን አማካኝነት ከወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች (ከአረቅጥ፣ ከድንቁላ፣ ጉንችሬ፣ ቋንጤ፣ መሀል አምባ እና ከሀዋሪያት) ለተውጣጡ 18 የአይ ሲ ቲ እና የኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ ት/ት ክፍል አሰልጣኝ መምህራንን ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በስልጠናውም ሂደት የተለያዩ ማሽነሪዎችና ኮምፒውተሮች ጥገና ተደርጎላቸዋል።

ስልጠናው የወሰዱ እነዚሁ አሰልጣኝ መምህራን ወደ ኮሌጆቻቸው ሲመለሱ በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለሌሎች አሰልጣኝ መምህራን እንዲያሰፉ ይደረጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *