የጥራት_አሀድ_አሰራርና_አደረጃጀት_መመሪያ_ላይ_ስልጠና_ተሰጠ

Spread the love

============================================

ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም፡ በአዲሱ የጥራት አሀድ አሰራርና አደረጃጀት መመሪያ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።

የስልጠናው በኮሌጃችን ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት በማረጋገጥ የተገልጋዮቻችንን እርካታ እንዲረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ ነው። የኮሌጁ ማህበረሰብ በየደረጃው ባሉ አደረጃጀቶች ውስጥ ተደራጅተው በነፃነት የሚወያዩበት፣ በተግባር ሂደት የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመተጋገዝ የሚፈቱበት፣ እርስ በእርሳቸው የሚማማሩበት እንዲሁም የተገኙ የምርጥ ተሞክሮዎችን ደግሞ ቀምረው ለሌሎች የሚያሰፉባቸውን የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በስልጠናውም ላይ የኮሌጁ አጠቃላይ ማኔጅመንት አባላት፣ የት/ት ክፍል ተጠሪዎች፣ ከየት/ት ክፍሎቹ የተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራንና ሰልጣኞች እንዲሁም ከተለያዩ የስራ ሂደቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *