#ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ የግንዛቤማስጨበጫ ስልጠናናየምክክር ወርክሾፕ
ሰኔ 29/2015 ዓ.ም፡ በዚህ አመት ኮሌጃችንን በሶላር ኢነርጂ ስልጠና ዙሪያ ድጋፍ እያደረገ የሚገኘው ADRA ETHIOPIA አዘጋጅነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና የምክክር ወርክሾፕ ተካሄደ።
በወርክሾፑ ላይ በታዳሽ ኢነርጂ በተለይም በሶላር ኢነርጂ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፅሁፎች በተለያዩ ምሁራን ቀርበው ሰፊ የግንዛቤ ስራ ተሰርቷል። በተጨማሪም በቀረቡ ፅሁፎች እና አጠቃላይ ተቀናጅቶ በመስራት ሂደት ባሉ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊዎች ሰፊ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በወርክሾፑ ላይ የፕሮጀክቱ የስትሪም ኮሚቴ አባላት፣ የተለያዩ የሴክተር መ/ቤቶች ኃላፊዎች፣ የሶላር እቃዎችን አቅርቦት ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ በክላስተራችን ስር የሚገኙ ኮሌጆች ዲኖች፣ የኮሌጃችን ዲኖችና የት/ት ክፍሎች ተጠሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።





Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0