የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዓመታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ!
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)
የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆችን ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ እና በኮሌጆች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራርና ትብብር ለማጠናከር ያለመ ዓመታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ አዘጋጅነት መሰጠት ተጀመረ።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው የቴክኖሎጂ እሴት ሰንሰለት ትንተና (Value Chain Analysis)፣ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action Research) እና የአእምሮአዊ ንብረት መብት (Patent Right) በሚሉ ፅንሰ-ሀሳቦች ላይ ነው። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።
በዚህም ከሁሉም የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች የተውጣጡ አሰልጣኞችና ም/ዲኖች፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች የትኩረት ዘርፍ መ/ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች፣ እና ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና ከወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል የተጋበዙ ባለሙያዎች በተሳታፊነትና በሙያዊ አስተዋፅኦ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ ስልጠናው የክላስተሩ ኮሌጆች የተቀናጀ አሰራርን ለማስፋፋትና የፈጠራና የምርምር ባህልን በማጠናከር የልማት ግቦች በተሻለ ውጤታማነት ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!





Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0