የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የባለድርሻ አካላት ውይይትና የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዓመታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ።
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)
የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክና የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዓመታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ።
የመድረኩ ዓላማ የቴ/ሙያ ዘርፍ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በጋራ መፈተሽ፣ የዘርፉን አፈጻጸም ለማሻሻል የሚያስችሉ የትብብር አማራጮችን መለየት፣ የሰልጣኞችን ቅበላ ቁጥር ማሳደግና የኮሌጁን አጠቃላይ ተቋማዊ አቅም ለማጎልበት ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ግንዛቤና መግባባት መፍጠር ነው።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን እንዳሉት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ትብብር ለቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ስኬት ያለውን ወሳኝ ሚና አጉልተው ያስቀመጡ ሲሆን በተለይም የሰልጣኞችን ቅበላ ቁጥር በማሳደግና ለስራ ገበያው ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
መድረኩን ያስጀመሩት የእለቱ የክብር እንግዳ የማኢ/ክ/ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እንዳሉት የቴ/ሙያ ዘርፍ ለኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ለስራ ፈጠራና ለሰው ኃይል ልማት ያለውን አስፈላጊነት በማጉላት፣ ተቋማት በቅንጅትና በትብብር በመስራት የስልጠና ውጤታማነትን ማሳደግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በመቀጠል ለመድረኩ የሚሆኑ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስትራቴጂያዊ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን እንዲሁም በመቀጠል በሰልጣኞች ቅበላ ሂደት ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ የጥናት ውጤት በአሰልጣኝ አንድነት አስናቀ አማካኝነት በተከታታይ ቀርበዋል።
በሰነዶች መነሻ ተሳታፊዎች ሰፊና ጥልቅ ውይይት አድርገዋል። የቴ/ሙያ ስልጠናን የስራ ገበያው ፍላጎት ጋር ማጣጣም፣ የሰልጣኞችን ቅበላ ቁጥር ለማሳደግ የህብረተሰብ ግንዛቤን ማሳደግ፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማጠናከር በሚሉ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ቀርበው ከተመከረባቸው በኋላ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ መድረኩ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዓመታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ በመሆኑ በክላስተር ደረጃ የሚከናወኑ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን፣ የኮሌጆችን የሰው ኃይል ሙያዊ ክህሎትና የተቋማዊ አፈጻጸም አቅም ለማሳደግ የሚያግዙ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የውይይቱን ውጤት ወደ ተግባር ለመቀየርና የተገኘውን መግባባት በተግባር ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የግብ-ስምምነት የመፈራረም ስራ የተሰራ ሲሆን ስምምነቱም በትብብርና በቅንጅት በመስራት የኮሌጁንና የክላስተር ኮሌጆችን የስልጠና አቅም ለማጠናከር፣ የሰልጣኞችን ቅበላ ቁጥር ለማሳደግና የቴ/ሙያ ዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሠረት የጣለ እንዲጥል ተደርጓል።
በአጠቃላይ በመድረኩ ላይ የማ/ኢ/ክ/የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሰለሞን ፋርሻ፣ የጉ/ዞን ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎች፣ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዲኖች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ተወካዮች፣ ከክላስተር ኮሌጆች የተውጣጡ አሰልጣኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ መሆን የቻሉ ሲህን መድረኩ የተቋማትን ትብብር ለማጠናከር፣ የጋራ የልማት አቅጣጫ ለመቅረጽ፣ የቴ/ሙያ ስልጠናን ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግና የክላስተር ኮሌጆችን አቅም ለመገንባት ጠቃሚ መድረክ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል::









Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0