#የ2019_የሥልጠና_ዘመን_የነባር_ሰልጣኞች_ስልጠናን_በተጠናከረ_ሁኔታ_የተጀመረና_የአዳዲስ_ሰልጣኞች_ምዝገባ_ደግሞ_እያካሄደ_ይገኛል።

Spread the love

#የ2019_የሥልጠና_ዘመን_የነባር_ሰልጣኞች_ስልጠናን_በተጠናከረ_ሁኔታ_የተጀመረና_የአዳዲስ_ሰልጣኞች_ምዝገባ_ደግሞ_እያካሄደ_ይገኛል።
=============================
መስከረም 27/2019 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የ2019 የነባር ሰልጣኞች ስልጠናን በተጠናከረ ሁኔታ የተጀመረ ሲሆን የአዳዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ ደግሞ እያካሄደ ይገኛል።

በቅርቡ የዓለም አቀፍ ስታንዳርድ የሆነውን ISO 21001፡2025 – Educational Organization Management System (EOMS) ሰርተፊኬት ያገኘው ኮሌጁ የሰልጣኞችን ፍላጎት ያማማከለና ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት ከፍተኛ አቅም ተፈጥሮለታል።

ከዚህ ስኬት ጋር ተያይዞ የነባር ሰልጣኞች ስልጠናንም በተሻለ ጥራትና አሰራር መሰጠት የጀመረ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎንም በተለያዩ ምክንያቶች ያልተመዘገቡ ነባር ሰልጣኞችን ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል። በመሆኑም ኮሌጁ እስከ አሁን ላልተመዘገቡ በተሰጠው የጊዜ ቀነ-ገደብ ውስጥ ተመዝግበው ስልጠናቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ያቀርባል።

በዚሁ አጋጣሚ ኮሌጁ የ2019 አዲስ ስልጠና ፈላጊዎች/ተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን እየገለፀ ኮሌጁ ለቀጣይ የሥራ ዓለም ዝግጁ የሚያደርጉ ምርጥ ምርጥ ሙያዎች ባለቤት ለመሆን የምትፈልጉ ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ መጥታችሁ እንድትመዘገቡና የዚህ ታላቅ እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪውን በደስታ ያቀርባል።

#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *