#ከተለያዩ_ባለድርሻ_አካላትና_የግሉ_ዘርፍ_ተቋማት_ጋር_በመተባበር_ተመራቂ_ሰልጣኞችን_ከሥራ_ጋር_የማስተሳሰር_ስራው_ተጠናክሮ_እየተከናወነ_ይገኛል።
============================
መስከረም 06/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከብሔራዊ የድጅታል መታወቂያ ጋር በመተባበር በ2018 ተመራቂ ሰልጣኞችን ከሥራ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል የምልመላ ፈተና አካሄደ።
የምልመላ ስራው በ2 ዙሮች በበይነ-መረብ የተካሄደ ሲሆን ከ60 በላይ ተመራቂ ሰልጣኞች የምልመላ ፈተናውን ወስደው አብዛኞቹ የማለፊያ ውጤት ማምጣት ችለዋል።
በቀጣይም ያለፉ ሰልጣኞች ተለይተው ለሥራው በቂ ዝግጅት እንዲኖራቸው በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አማካኝነት የአቅም ግንባታና የሥራ ዝግጅት ስልጠና እንደሚሰጣቸው ታውቋል። የስልጠናውን ሂደት ካጠናቀቁ በኋላም ተመራቂ ሰልጣኞቹ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገልጿል።
በአጠቃላይ ኮሌጁ ተመራቂ ሰልጣኞችን ከሥራ ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና የግሉ ዘርፍ ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር በትኩረት እየሠራ ይገኛል።
#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!




Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0