#የወልቂጤ_ፖሊቴክኒክ_ኮሌጅ_ሳተላይት_ካምፓስ_በተለያዩ_መስኮች_የበጎ_ፈቃድ_ድጋፍ_አደረገ።
===================
ጳጉሜ 4/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የህብር ቀንን እና የአዲስ ዓመት መባቻን በማስመልከት በተለያዩ መስኮች የበጎ ፈቃድ፣ የድጋፍና የእንክብካቤ ተግባራትን አከናውኗል።
ኮሌጁ በዕለቱ የማዕድ ማጋራት፣ የትምህርት መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ እና በወልቂጤ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ለሚገኙ ወላድ እናቶች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍን ጨምሮ ለጭራቁየት ቤተ-መፅሐፍት የበጎ ተግባራትን በተደራጀ መልኩ አከናውኗል። በአጠቃላይ ከ220 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስና የምግብ አስቤዛ ለ100 ተማሪዎችና ለ50 የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደርጓል።
በመርሃ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር፣ በከተማው በርካቶች የሚሳተፉበትና ለብዙ ወገኖች ተደራሽ የሆነ የበጎ ፈቃድ ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ ኮሌጅ የሰው ሃብትን ከማብቃትና ትውልድን ከመቅረጽ ባሻገር የተጠቃሚዎችን ቁጥር በማሳደግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝና ጥራት ያለው ስልጠና ከመስጠት ባሻገር በዘመን መለወጫ እና በህብር ቀን ያደረገውን የበጎ ተሳትፎ በማስፋትና በማጠናከር መቀጠሉ የሚደገፍ ነው ብለዋል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን በበኩላቸው እንዳሉት ኮሌጁ ከመደበኛ የስራ ኃላፊነቱ በተጓዳኝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተግባር እየተወጣ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ የተጀመረውን የበጎ ፈቃድ ተግባር በማጠናከር ለዜጎች የሚያስፈልገውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ኮሌጁ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በቀጣይነት እንደሚወጣ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ድጋፍ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በበኩላቸው በተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።






Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0