#ክልሉ_እንደሀገር_የተያዙ_የ5_ዓመት_ግቦችን_በላቀ_ደረጃ_ማሳካቱን_ተከትሎ_ዕውቅናና_ማበረታቻ_ሽልማት_አገኘ!!
ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም
የማ/ኢ/ክልል በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት እንዲሁም በሰራተኛና ማህበራዊ ዘርፍ የተከናወኑ አበይት ስኬቶችን በማስመዝገብ፣ ክልሉ ከተመሰረተ 3 ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሀገር የተያዙ የ5 ዓመት ግቦችን በላቀ ደረጃ በማሳካቱን ዕውቅናና ማበረታቻ ሽልማት ተቀብሏል።
በክልሉ የሚገኙ 3ቱ ቢሮዎች ታቅደው ሲተገበሩ የቆዩ 38 የሪፎርም ዘርመሎቾ መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የምዘና ሂደት በተቋማቱ ቀደም ሲል በእቅድ ሲተገበሩ የቆዩትን 38 የሪፎርም ማሻሻያ ስራዎች በዝርዝር በመገምገም እንደሆነም ተመላክቷል።
ሽልማቱና ማበረታቻው ተቋማቱ በህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ያስመዘገቧቸውን ለውጦች ለመለካት፣ ጠንካራ ጎኖቻቸውን ለማጠናከር እና በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸው ክፍተቶችን በመለየት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑ ታውቋል።
የተሰጠው ዕውቅናና ሽልማት፤ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ከተከናወኑ የዕቅድ ስኬቶች ባለፈ፣ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ስትራቴጂክ ግቦች ዙሪያ የተመዘገበውን አስደናቂ አፈጻጸም ጭምር ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።
የተመዘገበው ውጤት የሁሉም የጋራ ጥረትና ቅንጅት ውጤት በመሆኑ ክልሉ ካለው ተጨባጭ የመፈጸም አቅም አንፃር ተግባራትን በመቀናጀትና በትብብር በመሥራት ከዚህ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ተጠቁሟል።
ይህ ዕውቅናና ሽልማት ለተሻለ ስኬት መነሻ፣ የተመጣበትን መንገድ ለማየት የሚያስችልና የወደፊት ተግባራትን በቁርጠኝነት ለመፈጸም የሚያነሳሳ በመሆኑ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ለተሻለ ወጤት በትጋትና በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው መገለጹን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።





Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0