#የወልቂጤ_ክላስተር_ኮሌጆች_1041_ሰልጣኞችን_በጋራ_በደማቅ_ሥነሥርዓት_አስመረቁ።
=======================
ነሀሴ 02/2018 (ወልቂጤ)፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በጉራጌ ዞን የሚገኙ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች በ2018 ዓ.ም. በዲግሪ እና ከደረጃ 1 እስከ 5 ባሉ የሥልጠና መርሃ-ግብሮች ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ በአጠቃላይ 1,041 ሰልጣኞችን በጋራ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቁ።
የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ በወልቂጤ ክላስተር ሥር በሚገኙ ሰባት ኮሌጆች በተለያዩ የሥልጠና መስኮችና ደረጃዎች በመማር ሥልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን በአንድ የጋራ መድረክ ለማስመረቅ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የኢንዱስትሪ ተወካዮች፣ የተመራቂዎች ቤተሰቦችና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።
የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በዲግሪና ከደረጃ 1-5 ባሉ የሥልጠና መርሃ-ግብሮች 402 ሰልጣኞችን ማስመረቅ ችሏል። ይህም ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብቁ፣ ተግባራዊ እውቀትና ክህሎት የተላበሱ የሰው ኃይል ለማፍራት እያከናወነ ያለውን ሚና የሚያሳይ ነው።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልልና የጉራጌ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ለተመራቂ ሰልጣኞች፣ ለኮሌጆች አመራሮችና ለመላው ተመራቂዎች የማበረታቻ መልዕክትና የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል። አመራሮቹ ተመራቂዎች በሥልጠና ወቅት ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር በመተርጎም ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸውና ለሀገራቸው የሚጠቅም የሥራ እንቅስቃሴ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።
የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ በከፍተኛ የክልልና የዞን አመራሮች፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች አመራሮች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ የኮሌጆች ዲኖች፣ የተጋበዙ እንግዶችና በርካታ የተመራቂ ሰልጣኞች ቤተሰቦች ተገኝተዋል።






Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0