#እንኳን_ደስ_አለን!#የወልቂጤ_ፖሊቴክኒክ_ኮሌጅና_ሳተላይት_የካምፓስ_ለመላው_የኮሌጁ_ማህበረሰብና_የሚያስተላልፈው_የእንኳን_ደስ_አላችሁ_መልዕክት!!

Spread the love

#እንኳን_ደስ_አለን!
#የወልቂጤ_ፖሊቴክኒክ_ኮሌጅና_ሳተላይት_የካምፓስ_ለመላው_የኮሌጁ_ማህበረሰብና_የሚያስተላልፈው_የእንኳን_ደስ_አላችሁ_መልዕክት!!
==============
ሐምሌ 30/2018 (ወልቂጤ)፡ በማዕከላዊ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኘው የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በትምህርት ተቋማት የአሰራር ጥራት ስርዓት ISO 21001:2025 (Educational Organization Management System – EOMS) መስፈርትን በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ የምዘና ሂደቱን በብቃት አጠናቆ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ECA) የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘቱን በታላቅ ደስታና ኩራት እንገልጻለን።

ይህ ታላቅ ስኬት የኮሌጃችን አመራር፣ የመምህራን፣ የአስ/ ሰራተኞች፣ የተማሪዎች፣ የመንግስት አካላት፣ የክላስተር ኮሌጆችና የአካባቢው ማህበረሰብ የጋራ ጥረት፣ ቁርጠኝነትና ትብብር ውጤት ነው።

የተገኘው የISO 21001:2025 የብቃት ማረጋገጫ የኮሌጁ አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርት መሠረት እየተመሩ መሆናቸውን፣ ተማሪን ማዕከል ያደረገ የትምህርት ሥርዓት መገንባቱን፣ ቀጣይነት ያለው የጥራት መሻሻልን እና የደንበኞችና የባለድርሻ አካላት እርካታን ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።

በመሆኑም ይህ ውጤት የሁላችንም ድል በመሆኑ፣ ለመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ፣ ለማዕከላዊ ክልል፣ ለጉራጌ ዞን፣ ለአጋር ተቋማትና ለመላው የአካባቢው ህዝብ “እንኳን ደስ አላችሁ/አለን!” እያልን ልባዊ ደስታችንን እንገልፃለን።

ኮሌጃችን ከዚህ በኋላም በጥራት፣ በፈጠራ፣ በተጠያቂነትና በቀጣይ መሻሻል መርሆዎች ተመርቶ ለሀገራችን የሚያስፈልጉ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሥነ-ምግባራዊ የሙያ ባለቤቶችን በማፍራት ያለውን ኃላፊነት በበለጠ ትጋት ይወጣል።

#በድጋሚ_እንኳን_ደስ_አላችሁ!!🌷🥇👌

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *