Spread the love

#መደበኛው_የካይዘን_የፅዳት_መርሐ_ግብር_ተካሄደ!
==============================
ሐምሌ 28/2018 (ወልቂጤ)፡ በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ተቋማዊ ባህልን ለማሳደግና ለስራ ምቹ አካባቢን ለመፍጠርና የግቢ ፅዳትና ውበት በዘላቂነት ለማስጠበቅ ታስቦ በየ15 ቀናቱ የሚካሄደው መደበኛው የካይዘን (Kaizen) የፅዳት መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የፅዳት መርሐ-ግብሩ የኮሌጁ ማህበረሰብ የግቢውን ፅዳት በዘላቂነት ከመጠበቅ ባሻገር፣ የካይዘን (Kaizen) ፍልስፍናን በመተግበር ፅዳትን ባህል ለማድረግ፣ ማራኪ፣ ሳቢ እና ውብ በማድረግ ምቹና የስራና የመማር-ማስተማር ከባቢን ለመፍጠር እንዲሁም በተቋሙ እየተተገበረ ያለውን የISO ስታንዳርድ ትግበራ በላቀ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው። በመርሐ-ግብሩ ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና አስ/ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

#ለአረንጓዴው_የኢንደስትሪ_አብዮት_እንተጋለን!
#We_Stand_for_Green_Industrial_Revolution!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *