#የአረብ ሀገራት የስራ ስምሪት ላይ ያተኮረ የንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
ግንቦት 05/2016 ዓ.ም፡ ኮሌጃችን የአረብ ሀገራት የስራ ስምሪት #ክህሎት_መር እንዲሆን ታሳቢ ያደረገ የንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ።
በመድረኩ ላይ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ጁሀር፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፣ የክልሉ የብቃት ምዘና ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ራመቶ ቦካን በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም ሁሉም የጉራጌ ዞን ሴክተር መምሪያ ኃላፊዎች፣ በዞናችን ስር የሚገኙ 15 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች፣ የሥራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞችና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዞኑ የ2ቱ ሴክተር መምሪያ ኃላፊዎች፣ የቀቤና ልዩ ወረዳ የ2ቱ ሴክተር ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም በክላስተራችን ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ መነሻነት በእለቱ የክብር እንግዶች መሪነት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። ተሳታፊዎች ገንቢ አስተያየቶችና ግልፀኝነት የሚፈልጉ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ በተገኙ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም መድረኩ ለተግባሩ ውጤታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በማወቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የስራ መመሪያ በመስጠትና መግባባት ላይ በመደረስ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል።










Users Today : 8
Total Users : 7592
Views Today : 11
Views Yesterday : 14
Views Last 7 days : 165
Views Last 30 days : 445
Views This Month : 325
Views This Year : 4548
Total views : 31003
Who's Online : 0